Heading

 

መነሻ ገጽ

ዜና

ቃለ-ምልልስ

ለዕውቀትዎ

ስለ እኛ

ሰሞነኛ

አዲስ አበባ ማ/ቤቶች

ድሬዳዋ ማ/ቤት መምሪያ

ሮቢት ማ/ቤት መምሪያ

ዝዋይ ማ/ቤት መምሪያ

ጠቅላላ ሆስፒታል

ስፖርት

ክፍት የሥራ ቦታ (አዲስ)

ተፈላጊ አድራሻ

Language/ቋንቋ English/አማርኛ

 

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መልእክት

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በልማታዊ መንግስታችን የተነደፈውን የአምስት ዓመቱን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የተቋሙን ዓላማ ለማሳካት ታራሚዎችን በፍርድ ቤት ውሳኔ ተቀብሎ በመጠበቅ ማንኛውንም ታራሚ በቴክኒክና በልዩ ልዩ የሞያ ሥልጠናዎች በመደበኛና በቀለም ትምህርት እንዲሁም ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አቅም በፈቀደ መጠን የታራሚውን ሰብዓዊ መብት በመጠበቅ የመሠረታዊ ፍላጎት የሆኑትን ምግብ መጠለያ የሌሊት አልባሳት ነፃ የሕክምና አገልግሎት በተቋሙ የሕክምና ክፍሎችና በመንግስት ሆስፒታል አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ ተቋማችን ታራሚዎችን ሕግ አክባሪ አምራችና ጥሩ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ይጠበቅበታል፡፡

ተቋማችን ይህንን ዓላማውን ለማሳካት በአገራችን ለተገልጋዩ ሕብረተሰብና ለታራሚዎች ፈጣን ወጪ ቆጣቢ ቀልጣፋና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ B. P. R አጥንቶ ሙሉ ትግበራውን ከየካቲት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ቀጥሏል፡፡ በተቋሙ ያሉ የጥበቃ አባላትና የሲቪል ሠራተኞች በተሰማሩበት ሞያ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታላቅ ተነሳሽነትና ትጋት በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ የተፈለገውን ግብና ውጤት ለማምጣት የተቋሙ ሠራተኞች ብቻ የሚያከናውኑት ተግባር በቂ ስለማይሆን ታራሚዎችን በቀለም ትምህርት በልዩ ልዩ ሞያዎች አስተምረንና አሰልጥነን ወንጀልን የሚጠላ (የሚጸየፍ) ራሱንና ቤተሰቡን ብሎም ሀገሩን የሚጠቅም ዜጋ አድርጎ ለማውጣት የምናደርገውን ጥረት ሕብረተሰቡ እንዲያግዘንና እንዲረዳን ከማረሚያ ቤት ከላይ በተገለጸው መሠረት ታርመው የሚወጡ ታራሚዎች ከሕብረተሰቡ ጋር በሚቀላቀሉበት ጊዜ ቀድሞም ወንጀለኞች ነበሩ አሁንም ወንጀለኞች ናቸው ከማለት ይልቅ ታራሚዎችን አቅርቦ እያንዳንዱ የሕብረተሰብ ክፍል ሳያገላቸው የሚችለውን ድጋፍ በመሥጠት መልሶ እንዲያቋቁማቸውና ዳግም ወንጀል እንዳይሰሩ በወንጀል መከላከል ረገድ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በራሴና በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስም መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!!

 

 

ራዕይ

የፌዴራል ማ/ቤቶች አስተዳደር ታራሚዎችን በማረምና በማነጽ ሕግ አክባሪና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ተቋም ሆኖ ማየት ነው፡፡

ተልዕኮ

 • በፍርድ ቤቶች ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ መሰረት የሚላኩ ታራሚዎችን በመጠበቅ የተወሰነባቸውን ቅጣት ማስፈፀም፣
 • ለታራሚዎች ደረጃውን የጠበቀ የምክር አገልግሎት መስጠት ፣
 • የቀለም ትምህርትና ልዩ ልዩ የሙያ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ታርመውና ታንፀው የባህሪይና የአመለካከት ለውጥ ማምጣት፣
 • የተለያዩ መሠረታዊ አቅርቦቶችንና አገልግሎቶችን መስጠት፣ ከማረሚያ ቤት ሲወጡ በማቋቋም፣ ህግ አክባሪ፣ ሠላማዊና አምራች ዜጋ ሆነው ቀጣይ ህይወታቸው እንዲመሩ ማስቻል፣
 • ወንጀልን በመከላከል ሠላምና ፍትህን በማስፈን የበኩሉን ድርሻ መወጣትነው፣

እሴቶች

የፌዴራል ማ/ቤቶች አስተዳደር እንደ አንድ መንግሥታዊ ተቋም
በህዝብና በመንግሥት የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ መወጣት ይችል ዘንድ አገራዊ እሴቶችን ተቀብሎ ለተግባራዊነታቸው በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

 • ሕገ - መንግስቱንና ሕገ- መንግሥታዊ ስርዓቱን ማመንና መቀበል፣
 • ዲሞክራሲያዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ፣
 • ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ማስፈን፣
 • አድሎአዊነትና - ፍትሃዊነትን ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመዋጋት
 • በአንፃሩ በእኩልነት ፍትሃዊነትና በመልካም ስነ-ምግባር ላይ የተመሰረተ
 • አገልግሎት መስጠትን ዋነኛ እሴቱ አድርጎ ይንቀሳቀሳል፣
© 2011 FEDERAL PRISONS ADMINISTRATION